የከተማችን ነዋሪ እንድናቃልለት ከጠየቀን ችግሮች መካከል ቀዳሚ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በመንግስትና የግል አጋርነት አሰራር በጥናት ላይ ተመስርተን ፖሊሲ ፣ አሰራርና መመሪያ ቀርጸን ወደ ስራ ገብተናል፡፡
በዚህ የአሰራር ስርዓት የኦቪድ ግሩፕ የሰራቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች 60 ሺህ ቤቶችን በ3 ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ማጠናቀቅ የሚያስችል መሆኑን እምነት እንድንጥል አድርጎናል፡፡
ቤቶቹን ከመገንባት ባሻገር ለ200 ሺህ የከተማችን ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር እና ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽዖ የላቀ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ለፕሮጀክቱ መሳካት ድጋፍ ያደርጋል፡፡
ተቀናጅተን ስንሰራ ሩቅ የመሰሉ ይቀርባሉ፤ የከበዱ በርግጥም ይቀላሉ። በመፍጠርና በመፍጠን ለዘመናት የዘለቀውን የነዋሪዎቻችንን ጫናዎች በማቃለል ለመኖር ምቹ የሆነች አዲስ አበባን እውን እናደርጋለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ