የንፋስ ስልክ ላፍቶ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በክፍለ ከተማው የባለ ሶስት እግር ባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ህገ ወጥ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አሳወቀ፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስባቸው መንግስቴ በክፍለ ከተማው አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለይም በጀሞና ሰፈራ በሚባሉት አከባቢዎች በህገ ወጥ መንገድ ቢሮው ካስቀመጠው የአሰራር መመሪያ ውጪ እየሰሩ በነበሩ በ114 ህገ ወጥ የባለሶስት ባጃጆች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱም የቁጥጥር ስራውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ አባላቶች፣ የንፋስ ስልክ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ቅርንጫፍ፣ ትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ጋር ቅንጅታዊ አስራር በማጠናከር ቀጣይት ባለው መንገድ በሁሉም የክፍለ ከተማው አከባቢዎች የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ በህገ ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የባለሶስት እግር የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ከዚህ ህገ ወጥ ድርጊታቸው በመቆጠብ ትራንስፖርት ቢሮው ባወጣው መመሪያ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል።