(መስከረም 19/2015 ዓ.ም) ከነገ ወዲያ ቅደሜ መስከረም 21/2015 የኢሬቻ በዓል ሊከበር ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገ ይገኛል። ለኢሬቻ በዓል በሁሉም የከተማችን መግቢያ በሮች የሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ስለሚኖሩ ለጋራ ደህንነት፣ ሰላም እና ጸጥታ ሲባል ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴን መገደብ አስፈልጓል።
በዚሁ መሰረት ከነገ አርብ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ መስከረም 22/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኤጀንሲው ያሳውቃል።
የተጣለውን ገደብ ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ የእርምት ርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጭምር ኤጀንሲው ያሳስባል።
@TMA