ዛሬ ሀምሌ 15/2016 ከረፋዱ 5:45 አከባቢ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ 5 ሺህ ብር በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል።
ፍቅር ባርና ሬስቶራንት ድርጅት በተከለከለ ቦታ ተረፈ ምርትን እና ደረቅ ቆሻሻ በመጣላቸው ብር 50,000 እና ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት ብር 20,000 ተቀጥተው ቆሻሻውንም እንዲያነሳ ተደርገዋል።
እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ / የጥፋት አይነት ተ.ቁ 1.2 / መሰረት 50,000 ተቀጥቷል:: በጥቅሉ በልማት ኮርደሩ ላይ የደንብ መተላለፍ የፈፀሙ ሁለት ድርጅቶችና አንድ የጽዳት ማህበር በድምሩ 125,000 ብር ተቀጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከመንግሥት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በልማቱ ላይ በባለቤትነት እንደሚሳተፍ ሁሉ በመሰረተ ልማት ጠበቃ ዙሪያም በንቃት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን የሚቀጥል ይሆናል።