(ህዳር 26/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ፍሰት ሰላማዊና የተሳለጠ እንዲሆን በከተማ ደረጃ በተደረገ ውይይት ለትራፊክ አደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን በመለየት በተለይም የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ከተማዋ ዋና አውራ መንገድ እንዳይገቡ የሚከለክሉ ምልክቶችን በጥናት ላይ በመመስረት እየተከለ ይገኛል፡፡
ምልክቶቹ የተተከሉት በየካ፣ ቦሌ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማዎች ላይ ሲሆን በተለይም በሳሊተ ምህረት፣ ሚካኤል፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ የተባበሩት አያት አደባባይ መስመሮች ላይ የባጃጅ ተሽከርካራች አንዳይገቡ የሚያግድ ሲሆን በተጨማሪም ጎሮ፣ ጃክሮስ፣ መብራት ሐይል፣ እግዚሐቤር አብ፣ ዩኒቲ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ምልከቶቹ መተከላቸው ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች ከከባድ መኪናዎች እንዲሁም ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ጋር ግጭት በሚፈጥሩበት ጊዜ የተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች እንዳይከሰት ያግዛሉ አሽከርካሪዎችም በተፈቀደላቸው መስመር ብቻ እንዲቀሳቀሱ የሚያስችል መፍትሄ አላቸው፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመንገድ ተጠቃሚው ጥያቄ እና የትራፊክ ፖሊስ አባላት ጥቆማ ሌሎች ምልትና ማመላከቻዎችን ተከሏል፡፡