(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት ባለሙያዎች በቢሮው የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን በቴክኖሎጂ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የተሰጠው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ሲሆን ስልጠናው በትራንስፖርት ቢሮና ለተጠሪ ተቋማት ቴክኒክ ባለሙያዎች ለተውጣጡ 15 ባለሙያዎች ነው፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ጥናትና ስትራቴጂ ዳይሬክተር አቶ ኃይለማርያም ኃ/ሚካኤል ስልጠናው ፕሪማቬራ ሶፍትዌርን /primavera software/ መሠረት በማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አጠቃላይ ሁኔታ ለመምራት እና ለማስተዳደር እንዲሁም በቢሮው ለሚከናው የፕሮጀክት ስራዎች ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
ከተማዋ የተያያዘችውን የስማርት ሲቲ ትግበራ በትራንስፖርት መስክ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውጤታማ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር የሚያስችል ነው። ሰልጣኞችም ከስልጠናው በኋላ ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው ቢሮው በሚያከናውናቸው ታላላቅ ተግባራት ላይ ቀልጣፋ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲኖር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል ።
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://
ዌብ ሳይት:-www.aactb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!