(ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የሞተር ብስክሌት መንቀሳቀሻ ፈቃድን በዲጂታል መታወቂያ (Digital ID) መተግበሪያ ስራ ላይ ሊያውል በሂደት ላይ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።
የዲጂታል መታወቂያ የሚሰጥበት ጊዜ እስከ ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም በመሆኑ በከተማዋ የምንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳችሁን ጂፒ ኤስ ያስገጣማችሁበት ተቋም ጋር በመሄድ የዲጂታል መታወቂያውን እንድትወስዱ ኤጀንሲው በድጋሚ ያሳውቃል።
ከግንቦት 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር የዲጂታል መታወቂያ (Digital ID)ን ያልያዘ ሞተረኛ በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችል እና ያለ ዲጂታል መታወቂያ የምንቀሳቀሱት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጭምር ኤጀንሲው ያሳስባል።
ምንጭ:-ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ