አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፤ 2015 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አቅም ማጎልበትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የተቋማት አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ የአገልጋይነት ችግሮችን ለመፍታት በትንስፖርት ዘርፉ ለተሰማሩ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥርና ክትትልና ኢንስፔክሽን ለሚያደርጉ ባለሙያዎች በአገልጋይነት ስነምግባር ዙሪያ ከትራይቭ ኮንሰልቲንግ ከተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በስሩ የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን አቅም በተለያየ ደረጃ ለማጎልበት አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግና የትራንስፖርት ዘርፉ በቴክኖሎጂ ለማዘመን የዘርፉ አቅም ማጎልበትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የቢሮው የተቋም አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አብርሃም አድነው ገልፀዋል፡፡
በአገልግሎት ሰጪው ዘንድ የአገልጋይነት ስሜትን ለማስረፅ ቀጣይነት ያላቸው የስራ ላይ ስልጠናዋች ለመስጠት የታቀደ ሲሆን፤ በትራንስፖርት ዘርፉ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎችም በተሰማሩበት የስራ መስክ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝና የአሳተሳሰብና የባህሪ ለውጥ እንዲፈጥር የሚስችል መሆኑን ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ከስልጠናው በኋላም ሰልጣኞቹ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ተቋማዊ በሆነ መንገድ የተሻለና አዳዲስ አስተሳሰብን ወይም /Re thinking puplic transport as a driver of change a better city future/ እንዲኖር በማድረግ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የአሰራር ስርዓት በመፍጠር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በሰለጠነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎችም ከስልጠናው የተሻለ አቅም በማጎልበትና የተሻለ የባህሪ ለውጥ በመያዝ በተሰማራንበት ዘርፍ ፍፁም ሙያዊ ስነምግባር በመላበስ ህዝብና መንግስት የጣለብንን ኃላፊነት በግንባር ቀደምትነት ለማገልገል መዘጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ከትራንስፖርት ቢሮ ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ከአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ፣ ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የትራንስፖርት ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡