የሃገር መከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀል ሀገራችንን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ የወሰኑ ሠራተኞች ሽኝት ተደረገላቸው

የሃገር መከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀል ሀገራችንን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ የወሰኑ ሠራተኞች ሽኝት ተደረገላቸው

የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሰራተኞች የሃገር የመከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀል ሀገራችንን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ የወሰኑ ሠራተኞች ሽኝት ተደረገላቸው

የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቀድም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩና በተለያዩ የጦር የአገልግሎት መስኮች ያገለገሉ 60 ሠራተኞቹን ዛሬ ወደ ግንባር ሸኝቷል።

ሃገራዊ ጥሪን ተከትሎ መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑ የድርጅቱ ሰራተኞችም ደመወዝና ጥቅማጥቅሞቻቸው እንዲጠበቅላቸው፣ በድርጅቱ ያለባቸው ማንኛውም አይነት እዳ እንዲሰረዝላቸው፣ ለመጓጓዣ እና ለሌሎች ውጭዎች ይሆን ዘንድ የአንድ ወር ደሞዛቸው ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል፡፡

እንዲሁም ከእያንዳንዱ የዘማች ቤተሰብ አባል አንዱን የነፃ መንጃ ፈቃድ ተጠቃሚ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ በድርጅቱ የውጭ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በሚወጣበት ወቅት ቅድሚያ ለዘማች ቤተሰቦች እንዲሰጥ፣ እንዲሁም መላው የድርጅቱ ሰራተኛ የዘማች ቤተሰቦችን የመንካበከብ ሃላፊነት እንዳለበት የድርጅቱ ማኔጅመንት አባላት  ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ በሽኝቱ ወቅት እንደተናገሩት አሸባሪው የህወኃት ቡድን ከሌሎች ፀረ ኢትዮጵያ  ኃይሎች ጋር በመሆን ሀገራችንን ለማፈራረስ  ያለውን አቅም በሙሉ እየተጠቀመ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም የጥፋት ቡድኑ አላማ እንዳይሳካ ሁላችንም በምንችለው ሁሉ  መካላከል እና ሴረኞቹ እስኪጠፉ ድረስ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሰራተኞች ሃገራዊ ጥሪውን በመቀበል ያሳዩት ጀግንነት ለሌሎች ተቋማትም አርዓያ እንደሚሆን ቢሮ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገበየው ዋቄ በበኩላቸው ሀገራችን ለዘመናት በውጭ ወራሪም ሆነ በውስጥ ባንዳ ክብሯ ሳይደፈር የቆየው በጀግኖች አባቶቻችን ሲሆን የኛም ትውልድ  በጀግኖች ደምና አጥንት የቆየችውን ሀገር ከነ ሙሉ ክብሯ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ  በፍላጎታችሁ ወደ ጦር ግንባር በመዝመት ጀግናውን የሀገር መከላካያ ለመቀላቀል ለወሰናችሁ ሰራተኞቻችን ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

Leave a Reply