ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር የተናበበ የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ እንደሚደረግ ተገለጸ

ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር የተናበበ የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ እንደሚደረግ ተገለጸ

ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር የተናበበ የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ እንደሚደረግ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሰራተኞች ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር የተናበበ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ እንዴት ማሳለጥ እንደሚቻል ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል፡፡

በትራንስፖርት ዘርፍ በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እንዳይፈጠር ስራቸውን በትጋት እንሚሰሩ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ አገልግሎቱን በማዘግየት የቅሬታ ምንጭ እንዲሆን በሚጥሩ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወሰድ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አስረድተዋል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አካሉ አሰፋ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት በመሰራቱ ለውጦች መታየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ኃላፊው አክለውም ለውጡ ቀጣይነት እንዲኖረው ወቅታዊ መረጃዎችን በመለዋወጥ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ህገ ወጥ ሴረኞችን መከላከል ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ትራንስፖርት የሁሉም ኢኮኖሚ የደም ስር መሆኑን አቶ አካሉ ገልጸው በዘርፉ ወቅታዊ ሳንካዎች እንዳይገጥሙት ሁሉም ሰራተኛ በተሰማራበት ሙያ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አስገንዝበዋል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጃ ካሳ በበኩላቸው ቢሮው የመዲናዋን የትራንስፖርት ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ይህንን አገልግሎት በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ መላ ሰራተኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን ስነ ምግባር በመላበስ በትጋት እንዲሰሩ ጽ/ቤት ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ካላችበት ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አንድነታችንና ሰላማችንን በማጠናከር አገልግሎቱን ማሳለጥ ይገባል ብለዋል፡፡

Leave a Reply