“ኢትዮጵያን የተጋረጠባትን ጠላት በአንድነት እና በተባበረ ክንድ  እስከወዲያኛው  ታስወግዳለች “

“ኢትዮጵያን የተጋረጠባትን ጠላት በአንድነት እና በተባበረ ክንድ እስከወዲያኛው ታስወግዳለች “

በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በአባቶቻችን ዘመን ያልተሳካላቸው ሀይሎች ሚዲያቸውን በማዝመት ጭምር ቢያድሙብንም ኢትዮጵያውያን በጋራ ቆመን ምኞታቸውን ከንቱ እናደርጋለን ብለዋል።

የዴሞክራሲ ደቀመዝሙር ነን ባዮች ዴሞክራሲያዊ በሆነ መገድ የመረጥ ነው መንግሥት እያለ እኛ ያለስቀመጥ ነው ካልሆነ ብላው አሸንጉሊቶቻቸውን ለማስቀመጥ ይጥራሉ ብለዋል::

ኢትዮጵያውያን በጋራ ቆመን ኢትዮጵያን አክለን የምንሰጠው ምላሽ ለወዳጅ ብስራት ፤ለጠላት መርዶ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድነት እና በተባበረ ክንድ የተጋረጠባትን ጠላት እስከወዲያኛው ታስወግዳለች ብለዋል ።

አዲስ አበባ ተከባለች ይሉናል፤ አዲስ አበባ የተከበበችው በድንቅ ህዝቦቿ ነው፤ በሚጠብቋት ህዝቦቿ ነው፣ አዲስ አበባ የተከበበችው በጀግና ልጆቿ ነው ብለዋል።የአድዋ ልጆች ሆነን በአጋዋ ሊያስፈራሩን ይምክራሉ አድዋ ነጻነት፣ አገዋ ደግሞ እርዳታ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች አበቤ ።

ሊነጋጋ ሲል ይጨልማል አሁን ግን ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት እየነጋ ነው ድላችንን በታሪካዊው መስቀል አደባባይ በቅርቡ በድል እንዘምራለን ብለዋል።

የከተማዋ ወጣቶችም ለሀገራችን ነጻነት እንዝመት ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መከላከያን እንደግፍ ሀብታችንን እና ንብረታችንን ሀገር ለማዳን እናውል ብለዋል።

Leave a Reply