በመዲናዋ በሚገኙ 52 ሺህ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶች ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ ተከናወነ

በመዲናዋ በሚገኙ 52 ሺህ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶች ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ ተከናወነ

በመዲናዋ በሚገኙ 52 ሺህ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶች ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ ተከናውኗል፡፡

የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ሀብቶች ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

ከሳር ቤት አደባባይ እስከ ካርል አደባባይ  የትራንስፖርት ቢሮው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ጉብኝቱ ተከናውኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት በከተማ በስድስት ክፍለ ከተሞች ማለትም በአራዳ፣ በቦሌ፣ በየካ፣ በቂርቆስ፣ በኮልፌ ቀራንዮ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

እስካሁን በከተማዋ 52 ሺህ ሀብቶች ላይ ልዩ ኮድና ስያሜ የመለጠፍ ስራ ተሰርቷል፡፡

Leave a Reply