የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የቁጥጥር ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥና ሙያዊ ስነ ምግባር ዙሪያ በአዲስ አበባ ስራ አመራር አካዳሚ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07/ 2015 ዓ/ም፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በስሩ ለሚገኙ አጠቃላይ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የቁጥጥር ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥና ሙያዊ ስነ ምግባር ዙሪያ በአዲስ አበባ ስራ አመራር አካዳሚ የስልጠና ባለሙያዎች ለመጀመርያ ዙር 100 ሰልጣኞች ለአምስት ቀናት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በትራንስፖርት ቢሮ የጥናትና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የተቋማት አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ አብርሃም አድነው በ2015 በጀት ዓመት በእቅድ ከተያዙት ስልጠናዎች መካከል አንዱ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም በማሳደግ የሠራተኛውን ሙያዊ ስነ ምግባርና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሳደግ ነው ብለዋል።

ቢሮው በተያዘው በጀት አመት ተቋማዊ አቅምን ለመገንባትና በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ተከታታይነት ያላቸው ሙያዊ ስልጠናዎችን መስጠት መቻሉን አቶ አብርሀም ገልፀዋል።

የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስምሪትና የቁጥጥር ባለሙያዎች በዘርፋ ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊው ሙያው የሚጠይቀውን ሙያዊ ስነ- ምግባር ተላብሶ በቅንነት አገልግሎት ለመስጠት ለባለሙያው ትልቅ አቅም መገንቢያ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል::

በመጨረሻ ምን ውጤትና ለውጥ አመጡ የሚለውን በስራ ገበታቸው በሂደት በመከታተል የፋይዳ ግምገማ በማድረግ በጥናት ምን ውጤት መጣ የሚለው የሚታይ እንደሆነ በመግለፅ ሁሉም ሠልጣኞች ከስልጠና በኋላ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ሲሉ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply