አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ታስበው እንደሚውሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

መንግስት የ2015 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ታስበው እንደሚውሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ በሰጡት መግለጫ፦ በ2014 ዓ.ም የታዩ ስኬቶችንና የገጠሙ ፈተናዎችን መነሻ በማድረግ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ታስበው ይውላሉ ብለዋል።

እየተጠናቀቀ ያለው 2014 ዓ.ም ህውሃት፣ አልሻባብ እና ሸኔን ጨምሮ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ኢትዮጵያን በከፍተኛ ደረጃ የፈተኑበት ዓመት ቢሆንም በብዙ ስኬቶች የታጀበም ዓመት ነበር ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፦ ካለፉ ችግሮች ለመማርና የነበሩ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መጪው አዲስ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል።

አምስቱ የጳጉሜ ቀናት “#ጳጉሜን_በመደመር” በሚል መሪ ቃል ታስበው እንዲውሉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኗል ብለዋል።

ለአምስቱ ቀናት የተለያየ ስያሜ እንደተሰጣቸው የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህም መሰረት፦

👉 ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን

👉 ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀን

👉 ጳጉሜ 3 የሰላም ቀን

👉 ጳጉሜ 4 የአገልጋይነት ቀን እና

👉 ጳጉሜ 5 የአንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ ይውላል፡፡

Leave a Reply