የመረጃ ስርዓትን ማዘመን የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተገለፀ

የመረጃ ስርዓትን ማዘመን የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተገለፀ

በከተማዋ ምቹ፣ አስተማማኝና ተደራሽ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ረገድ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ ለዘርፉ ሙያተኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

በብሉምበርግ ኢንሼቲቭ አለም አቀፍ አጋር ድርጅት የተዘጋጀ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከመስከረም 12 እስከ 13/2014 ዓ.ም በጂ አይ ኤስ ዙሪያ በፍሬንድሺፕ ሆቴል በቨርቹዋል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አስተባባሪ ኢንጂነር ዮሐንስ ለገሰ እንደተናገሩት የመረጃ አያያዝን፣ አሰጣጥ እና አጠቃቀምን በማዘመን የትራፊክ አደጋን መቀነስ ያስችላል ብለዋል፡፡

የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ለማዘመን ጂአይኤስ ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ያስታወሱት ኢንጂነር ዮሐንስ የመንገድ ደህንነቱን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ረገድ አለም አቀፍ ተቋሙ የትራንስፖርት ዘርፉን ተዋንያን ለማብቃት በተከታታይነት የአቅም ማጎልበቻ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በብሉምበርግ ኢኒሼዬቲቭ ፎር ግሎባል ሴፍቲ የመንገድ ደህንነት መረጃ አስተባባሪ ወ/ሮ ሜሮን ጌታቸው በበኩላቸው የትራፊክ አደጋ መረጃዎች ሥርዓት ማዘመን ለትራፊክ ግጭት መፍትሔ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ግጭቱን ለመቀነስ የተደራጁ መረጃዎችን በጂዮግራፊካል ኢንፎርሜሽን ሲስተም(ጂ አይ ኤስ) በመጠቀም መያዝ፣ መስጠትና መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

ይህን በመተግበር በትራፊክ አደጋ ና ዙሪያ ያሉ የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን በማቀላጠፍ የመንገድ ደህንነት ስራዎችን ለማረጋገጥ እንደሚቻል ወ/ሮ ሜሮን ጌታቸው አስታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ ሜሮን አክለውም የትራፊክ ግጭትን ለመቀነስ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትራንስፖርት ቢሮ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ለተውጣጡ የመንገድ ደህንነት ሙያተኞች እና አመራሮች አቅም ማጎልበቻው እየተሰጠ ነው፡፡

Leave a Reply