በከተማዋ የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተናገሩ

በከተማዋ የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተናገሩ

በከተማዋ የትራንስፖርት እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተናግረዋል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት መገናኛ ተርሚናል ያነጋገራቸው አቶ አፈወርቅ ከፍያለው  በአስተባባሪዎች እየተሰራ ባለው ስራ የአውቶቡሶች ምልልስ እየጨመረ መምጣቱን አውስተው አስተባባሪዎች ሰልፍ  ወዳለበት አካባቢ ተሽከርካሪ በመመደብ እጥረቱን ለመቀነስ የተሰራው ስራ የሚያስመሰግን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በተለይ በምሽት ወቅት የትራንስፖርት እጥረት እንደሚያጋጥም አቶ አፈወርቅ ገልጸው በአሁኑ ወቅት እጥረቱን ለመቀነስ በተወሰደው የማስተባበር ስራ የትራንስፖርት ቆይታ ጊዜን በአማካይ በ25 ደቂቃ ትራንስፖርት እያገኙ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

አቶ አፈወርቅ አክለውም በሰሞኑ የታየው አገልግሎት ወደተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገር የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የሰዓት አጠቃቀም ለትራንስፖርት አጠቃቀም አመቺ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

አቶ ተገኝ በቀለ በበኩላቸው ትምህርት ቤት መከፈትን ተከትሎ የትራንስፖርት እጥረት መባባሱን ጠቁመው የትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም እጥረቱ ላይ ተጨማሪ ተግዳሮት ፈጥሯል ብለዋል፡፡

በመንገዶች መበላሸት ምክንያት እስከአንድ ሰዓት ድረስ በመንገድ ላይ ጊዜ የሚወስድበት አጋጣሚ መኖሩን አቶ ተገኝ ገልጸው እጥረቱ ከዚህ የበለጠ እንዳይባባስ የትራንስፖርት ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የታክሲ ሾፌር የሆኑት አቶ ጌታቸው ተስፋእግዚ በሰሞኑ ሰልፉን ለመቀነስ የተሰራው ስራ አበረታች ቢሆንም በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የመንገድ መዘጋጋት መሻሻል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

በተለይ በምሽት ሰዓት ትራንስፖርት ተጠቃሚ እያለ ታክሲዎች በስራ ገበታቸው የማይገኙበት አጋጣሚ መኖሩን ጠቁመው ከዞናዊ ስምሪት ውጭ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ቀጣይነት ባለው ክትትልና ቁጥጥር ስራ ከተሰራ የተሻለ ለውጥ እንደሚመጣ  ገልጸዋል፡፡

የመንገድ መዘጋጋትን ለመቀነስ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጥ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም አገልግሎቱ የተቀላጠፈ እንዲሆን አሽከርካሪዎችና ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የአስተባባሪዎች ትዕዛዝ በቀናነት መቀበል እንደሚገባ ጌታቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply